• Version
  • Download 0
  • File Size 0.18 KB
  • File Count 1
  • Create Date June 18, 2021
  • Last Updated June 18, 2021

በለጠ

ለ ኢትዮጵያ ሳምንት ፈስቲቫል ላይ የሚቀርቡ ትዕይንታዊ እና ቁሳዊ ነገሮች ዝርዝር
የፌስቲቫሉ አይነት የማቅረቢያ ቦታ ብዛት ይአፌስቲቫሉ አቀራረብ ዝርዝር ማሳሰቢያ ዝግጅት ማጠናቀቂያ ቀነ ገደብ
1 ትዕይንታዊ ክንውኖች በፌስቲቫሉ ቦታ ላይ የክልሉን ባህል እና ገፅታ በደንብ ሊገልፁ የሚችሉ የተመረጡ ትዕይንቶች ይየሚቀርቡ የትዕይንት አይነቶች
* ባህላዊ የቡና አፈላል ስነስርዓት
* ባህላዊ የሰርግ ስነስርዓት
* ባህላዊ የማህበረሰብ በዓላት አከባበር (ኢሬቻ፣ አሸንዳ፣ ሻደይ፣ ፊቼ ጨምበላላ ወዘተ)
* ባህላዊ የግጭት አፈታት ስነስርዓቶች
* ባህላዊ የፋሽን ትርኢት
ከየክልሉ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት በባህላዊ መንገድ ያጌጡ ፋሽን ሾው የሚያሳዩ ሰዎች ተመርጠው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
የሚቀርቡት ትዕይንታዊ ክንውኖች
* ባህላዊ ይዘታቸውን የጠበቁ
* ፈስቲቫሉን በሚመጥን ልክ ዝግጅት የተደረገባቸው
* ረጅም ሰዓትን የማይወስዱ መሆን ይጠበቅባቸዋል
ሚያዚያ 27 ድረስ ትዕይንታዊ ክንውኖቹ ተመርጠው ዝግጅት መጀመር አለበት
2 ባህላዊ ምግብ እና መጠጦች በፌስቲቫሉ ቦታ ላይ የተፈለገውን ያህል ባህላዊ የሆኑ ክልሉን የሚወክሉ በንፅህና የተዘጋጁ እና ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችሉ ምግብና መጠጦች መሆን አለባቸው። በተመረጠ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ይሆናል።

የሚዘጋጁት ምግብና መጠጦች፣ ንፁህ እና ባህላዊ በሆነ ማቅረቢያ መቅረብ ይኖርባቸዋል።

3 ለሽያጭ የሚቀርቡ ባህላዊ መገለጫዎች በፌስቲቫሉ ቦታ ላይ የተፈለገውን ያህል ለሽያጭ የሚቀርቡ ባህላዊ መገለጫዎች አይነት
* ባህላዊ አልባሳት
* ባህላዊ ጊጣጌጦች
* ቅርፃቅርፆች
* በአነስተኛ መጠን ታትመው የተዘጋጁ መልከዓ ምድራዊ ገፅታዎች፣ ባህላዊ አኗኗር፣ ማህበረሰባዊ ቱሩፋቶች፣ የቱሪዝም መስህቦችን እና መሰል ሀብቶችን የሚያሳዩ ፎቶዎች።
* ሁሉም ለሽያጭ የሚቀርቡ ቁሳቁሶች የክልሉ መገለጫ እና ባህላዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ብቻ መሆን አለባቸው ለሽያጭ የሚቀርቡት መገለጫዎች በውል ተለይተው ግንቦት 3 ድረስ መታወቅ ይኖርባቸዋል።